ማረጥን ተከትሎ የሚመጣ ድባቴ
ማረጥ የሆርሞኖች ለውጥ ሂደት ሲሆን ይህም በሴቷ ከ40ዎቹ አጋማሽ እስከ 40ዎቹ መገባደጃ ላይ የሚጀምር ነው። እነዚህ ለውጦች ስሜትን እና አጠቃላይ የአእምሮ ጤናን የመጉዳት እና ለድብርት የመጋለጥ እድልን ይጨምራሉ። ማረጥ በራሱ ጉልህ የሆነ የህይወት ሽግግር ስለሆነ አንዳንድ ጊዜ የስሜት መለዋወጥ እና ለጭንቀት መዳረግ በጣም የተለመደ ነው። በሌላ በኩል ድባቴ ይበልጥ አሳሳቢ ሁኔታ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት 30% የሚሆኑ ሴቶች በዚህ ጊዜ ድባቴ ያጋጥማቸዋል።
እንዲያውም በዚህ የሽግግር ወቅት ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ ከነበሩት ጊዜያት ይልቅ ለድባቴ የመጋለጥ እድላቸው በማረጥ ወቅት ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ በማረጥ ወቅት ድባቴን ማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል; ምክንያቱም ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ ከሌሎች የማረጥ ምልክቶች ጋር ስለሚጣመሩ ነው።
ስለዚህ በማረጥ ወቅት መለስተኛ ስሜታዊ ወይም ሥነ ልቦናዊ ተግዳሮቶች እንኳን ቢሆኑም ሐኪምን ለማማከር ትክክለኛ ምክንያቶች ናቸው።
የመንፈስ ጭንቀት ምልክቶች በአብዛኛው የሚከሰቱት በቅድመ ማረጥ ወቅት ነው። የሽግግር ደረጃዎች ወደ ድባቴ ያመራል። ይህም በተለይ በማረጥ ጊዜያት ውስጥ በስሜት እና በጤንነት ላይ ለውጦችን መከታተል በጣም አስፈላጊ ያደርገዋል።
ሴቶች በማረጥ ወቅት ለምን ድባቴ ያጋጥማቸዋል
የድባቴ ምልክቶችን የሚጨምሩ በፔርሜኖፓውስ(የወር አበባ ከመቋረጥ በፊት ያሉት ግዚያት) ወቅት ብዙ ምክንያቶች አሉ። እነዚህም የቫሶሞቶር ምልክቶች፣ የወር አበባ መቋረጥ አይነት፣ ሆርሞኖች፣ የህይወት አስጨናቂዎች ሁናቴዎች እና ቀድሞ Depression(ድባቴ) ታክማ የምታውቅ ከሆነ የመከሰት እድሉን ከፍ ያድርገዋል ።
- Vasomotor ምልክቶች፡- እንደ ሌሊት ላብ ወይም ትኩሳት ያሉ ምልክቶች የቫሶሞቶር ምልክቶች (VMS) ይባላሉ። እስከ 80% የሚደርሱ ሴቶችን ይጎዳል እና እነዚህ ምልክቶች በ በማረጥ ግዚያት ውስጥ በብዛት ይከሰታሉ እና መደበኛ የእንቅልፍ ሁኔታን በእጅጉ ሊያዛቡ ይችላሉ። ሴቶች በአብዛኛው በእንቅልፍ መዛባት ምክንያት ለድባቴ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
- የማረጥ ጊዜ እና አይነት፡- በተፈጥሮ በእድሜ ሂደት ምክንያት ተፈጥሯዊ ማረጥ ይከሰታል ነገር ግን በህክምና ሂደት ውስጥ ሁለቱም ኦቫሪዎች(እንቁልጢ) ሲወገድ የቀዶ ጥገና ማረጥ ይከሰታል። ይህም ጥናቶች እንደሚያሳዩት የቀዶ ጥገና ማረጥ ለአንድ ሰው ከማረጥ ጋር ተያይዞ ለሚከስት ድባቴ የመጋለጥ ትልቅ አደጋን ይጨምራል።
- ሆርሞኖች፡- እንደ ኢስትሮጅን፣ ፕሮጄስትሮን እና ቴስቶስትሮን ያሉ ሆርሞኖች በማረጥ ወቅት እየቀነሱ ይሄዳሉ። ይህም የሆርሞኖች መለዋወጥ በማረጥ ወቅት ለሚከሰት ድባቴ እንዲከሰት አስተዋጽኦ ያደርጋል።
- አስጨናቂ የህይወት ክስተቶች፡ ማንኛውም የህይወት አስጨናቂ ግዚያት የድብርት ምልክቶችን የመቀስቀስ አቅም አላቸው። አስጨናቂ የህይወት ክስተቶች የግብረ-ሥጋ ግንኙነት መቀነስ እንዲሁ የድባቴ ምልክቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ።
- የቀድሞ ሕክምና ታሪክ፡- በማረጥ ወቅት ዋነኛው ለድብርት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች ውስጥ ከዚህ ቀደም ድባቴ (Depression) ታክመው ከነበረ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ የሚመጣ ድባቴ(postpartum depression) ታሪክን ያጠቃልላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከዚህ በፊት የ depression ታሪክ ያለባቸው አዲስ ከሚጀምራቸው የበለጠ በማረጥ ወቅት ለሚከሰት ድባቴ እድሉ ከፍ ያለ ነው።
ማረጥ እና የድባቴ ምልክቶች
በማረጥ ወቅት የድባቴን ምልክቶች ማወቅ እርዳታን ለማግኘት ወሳኝ ነው። በማረጥ ወቅት አንዳንድ የተለመዱ የድባቴ ምልክቶች:-
- ቁጡነት ወይም ብስጭት፦ በትናንሽ ነገሮች ላይ ከወትሮው በበለጠ እየተናደዱ ወይም እየተበሳጩ ሊገኙ ይችላሉ።
- ድካም እና ዝቅተኛ ጉልበት፦ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እና በተለመደ የዕለት ተዕለት ክንዋኔዎችን ውስጥ ለመሳተፍ እና ለመተግበር ከባድ መሆን። ከበቂ እረፍት በኋላ እንኳን የድካም ስሜት ወይም ጉልበት ማጣት።
- የማያቋርጥ ሀዘን፦ አብዛኛው ቀን ሀዘን ወይም ባዶነት መሰማት በየቀኑ ማለት ይቻላል።
- የፍላጎት ማጣት፦ ለመዝናናትም ሆነ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ላይ ፍላጎት ማጣት።
- Brain fog፡- እንደ ደካማ የማስታወስ ችሎታ፣ የዘገየ አስተሳሰብ እና ትኩረትን የመሰብሰብ ችግር ፣ ብዙ ጊዜ እንደ ጭንቀት ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ የሆርሞን ለውጦች
- የእንቅልፍ ችግሮች፡- እንቅልፍ ማጣት ወይም ከመጠን በላይ መተኛት።
- የምግብ ፍላጎት ለውጦች፡- የሚታይ ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር።
- የማተኮር ችግር፡ የመረበሽ ወይም ውሳኔ የማድረግ ችግር
- ዋጋ ቢስነት ስሜት፡- ከመጠን ያለፈ የጥፋተኝነት ስሜት ወይም የከንቱነት ስሜት መሰማት።
- አካላዊ ምልክቶች፡- ግልጽ የሆነ አካላዊ ምክንያት ሳይኖር ህመሞች፣ ወይም የምግብ መፈጨት ችግሮች ፤ ፍራቻ
- ስለ ሞት ወይም ራስን የማጥፋት ሀሳቦች፡- በተደጋጋሚ ማሰብ።
- ለወሲብ ፍላጎት ማጣት ወይም በወሲብ እርካታ ለማግኘት መቸገር
- የሰውነት ከመጠን በላይ መሞቅ እና የሌሊት ላብ
እነዚህ ምልክቶች ከታዩ፣ የባለሙያ እርዳታ መፈለግ በጣም አስፈላጊ ነው። ማረጥን ተከትሎ የሚመጣ ድባቴ ከባድ እና ውስብስብ ቢሆንም; ሊታከም ግን ይችላል።
ከማረጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ድባቴን እንዴት እንቆጣጠር
በማረጥ ወቅት ድባቴን መቆጣጠር የአኗኗር ለውጦችን፣ ሕክምናዎችን እና የስሜት ድጋፍን ያካትታል። እነዚህን ለውጦች ማካተት፡-
- የአኗኗር ለውጦች፡- መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሰውነት ተፈጥሯዊ ስሜትን ከፍ የሚያደርግ ኢንዶርፊን በመልቀቅ ስሜትን ሊያስተካክል ይችላል።
- ጤናማ አመጋገብ፡- በፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ስስ ፕሮቲን እና ሙሉ በእህል የበለፀገ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አጠቃላይ ደህንነትን ያሻሽላል።
- በቂ እንቅልፍ፡- መደበኛ የእንቅልፍ መርሃ ግብር በመጠበቅ እና የተረጋጋ የእንቅልፍ አካባቢን በመፍጠር ጥሩ እንቅልፍ ለማኘት መሞከር ላይ ቅድሚያ መስጠት።
- ጭንቀትን መቀነስ፡ እንደ ዮጋ፣ ማሰላሰል፣ ወይም ጥልቅ የመተንፈስ ልምምዶችን የመሳሰሉ የጭንቀት ማስታገሻ ዘዴዎችን መለማማድ።
- አልኮል መጠጦችን እና እጾችን መገደብ
- የሆርሞን ምትክ ሕክምና (HRT)፡- HRT የሆርሞን መጠንን ሚዛን ለመጠበቅ እና ድባቴን ጨምሮ አንዳንድ የማረጥ ምልክቶችን ለማስታገስ ይረዳል።
- ፀረ-ጭንቀቶች(Antidepressant) መድሀኒቶች፡- እንደ ሴሮቶኒን፤ (SSRIs) ያሉ መድኃኒቶች ድብርትን ለመቆጣጠር ይረዳሉ።
- ቴራፒ፡ ከአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር መነጋገር ጠቃሚ ድጋፍ እና መልሶ ለመቋቋምም የሚረዱ ግንዛቤዎችን ማግኘት ወሳኝ ነው።
- ስሜታዊ ድጋፍ፡- የድጋፍ ቡድኖች፡ ማረጥ ወይም የመንፈስ ጭንቀት ድጋፍ ቡድንን መቀላቀል የማህበረሰቡን ስሜት እና የጋራ ልምድን ይሰጣል።
- ክፍት ግንኙነት፡- ስለ ስሜቶችዎ ከምትወዷቸው ሰዎች ጋር ተነጋገሩ። ጠንካራ የድጋፍ አውታር መኖሩ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።
- ራስን መንከባከብ፡- በማንበብ፣ ወይም ከጓደኞች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ደስታን እና መዝናናትን የሚፈጥሩ ተግባራት ላይ ጊዜ ማሳለፍ።




