የድባቴ ህመም ምንድን ነው??
ድባቴ በአንድ ሰው አስተሳሰብ ፣ ስሜት እና ተግባር ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሀዘን ፣ ገለልተኛነት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት የሚፈጥር የአእምሮ ሁኔታ ነዉ:: ድባቴ በየአመቱ ሚሊዮን ያህል ሰዎችን የሚያጠቃ የተለመደ ሁኔታ ነው። ከ10 ሰዎች ሶስቱ በድባቴ ህመም ተጠቂ ናቸው::
የድባቴ መንስኤዎቹ በተለያዩ ሰዎች መካከል ብዙ ሊለያዩ ይችላሉ::አስጨናቂ የልጅነት ገጠመኞች፣ የሕይወት ክስተቶች፣ የጤና እክሎች፣ እና ሌሎችም መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ::
የድባቴ ህመም ምልክቶች ምንድናቸው??
- ሀዘን፣ጭንቀት ፣ ተስፋ የመቁረጥ ወይም ‘ባዶነት’ ስሜት
- በፊት በሚደሰቱባቸው ነገሮች ደስታ/ፍላጎት ማጣት
- የድካም እና ሃይል የማጣት ስሜት
- ያልተገባ የጥፋተኝነት ስሜት ፣ጥቅም አልባነት ስሜት
- የትኩረት ማጣት ወይም አለማስተዋል
- የእንቅልፍ እጦት ወይም ከልክ በላይ ማንቀላፋት
- የምግብ ፍላጎት መዛባት
ድብርት እየተሰማዎት ከሆነ ይህን አስቸጋሪ ስሜት ለመቋቋም ራስን ለመጉዳት ወይም ስለ ራስን ለመግደል ሊያስቡ ይችላሉ። እነዚህ ሀሳቦች መቆጣጠር አስቸጋሪ ሊሆን ወይም በጣም ሊያስፈራ ይችላል::
ድባቴን እንዴት እናሸንፍ??
የድባቴ ህመም አሳሳቢና አስጨናቂ ሊሆን ይችላል; ነገር ግን ራስን ለመርዳት የሚያስችሉ እርምጃዎች አሉ::
- የሚቀርቡት የቅርብ ጓደኛ ወይም ዘመድ ጋር ማውራት
- ህሳቦትን እና ስሜቶትን መጻፍ
- አዳዲስ ነገሮችን ወይንም ልምዶችን
- መሞከር
- እርዳታ መጠየቅ
የተጠቀሱትን ምልክቶች ቢያንስ ለሁለት ሳምንት ያክል እራስዎት ላይ ካዩ ወይም በማንኛውም ጊዜ እራስዎን የመጉዳት ወይም ራስን የማጥፋት ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ ሁልጊዜም የስነ አእምሮ ሕክምና ባለሙያ እርዳታ መጠየቅ ይኖርብዎታል!!
"ማንኛውም ሰው ድባቴ ሊያደርስበት ይችላል ቢሆንም ድባቴ በቀላሉ ሊታከም ይችላልበማንኛውም ጊዜ የድባቴ ምልክቶች ካሎት የጤና ባለሙያ ያናግሩ እርዳታ በፍጥነት ካገኙ በፍጥነት ማማለጥ ይችላሉ::"




