1. የደም ግፊት (Hypertension) ምንድን ነው?
የደም ግፊት ማለት ልብ ደምን ወደ መላው የሰውነት ክፍል በደም ቧንቧዎች በኩል በሚገፋበት ጊዜ በደም ቧንቧ ግድግዳዎች ላይ የሚፈጠረው ግፊት ከመጠን በላይ ሆኖ ሲገኝ ነው።
2. "ጸጥተኛው ገዳይ" (The Silent Killer)
የደም ግፊት ብዙ ጊዜ "ጸጥተኛው ገዳይ" በመባል ይታወቃል። ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ምንም አይነት ግልጽ የሆነ ምልክት ሳያሳይ ለዓመታት በሰውነት ውስጥ ሊቆይ ይችላል። ሰዎች ግፊታቸው በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ወይም በድንገት ከባድ የጤና ችግር እስኪፈጥር ድረስ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለባቸው ላያውቁ ይችላሉ። ስለዚህ የደም ግፊት ክትትል ማድረግ ወሳኝ ነው።
3. የተለመዱ ምልክቶች (Common Signs & Symptoms)
ምንም እንኳን በሽታው በጸጥታ ቢጀምርም፣ አንዳንዶቹ ታካሚዎች የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ፡
- ጠንከርያለ የራስ ምታት (በተለይ ከጭንቅላትጀርባ)
- የዐይንብዥታ ወይም የእይታ መዛባት
- የማዞርእና የድካም ስሜት
- የልብምት በፍጥነት መምታት ወይም መረበሽ
- የትንፋሽእጥረት
4. ድንገተኛ የደም ግፊት መጨመር (Hypertensive Urgency vs. Emergency)
የደም ግፊት መጨመር በሁለት ይከፈላል፡
- Hypertensive Urgency (አስቸኳይየደም ግፊት መጨመር): የደም ግፊት መጠን በጣም ከፍተኛ (ከ 180/120 mmHg በላይ) የሚደርስበት ነገር ግን በዋና ዋና የሰውነት ክፍሎች (ልብ፣ አንጎል፣ኩላሊት) ላይ አጣዳፊጉዳት ያልደረሰበት ሁኔታ ነው። ይህ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በህክምና መስተካከል አለበት።
- Hypertensive Emergency (አስከፊድንገተኛ የደም ግፊትመጨመር): የደምግፊቱ ከመጠን በላይ ከመጨመሩም በላይ በዋና ዋና አካላት ላይ አጣዳፊ ጉዳት ማድረስ ሲጀምር ነው። ይህ የህይወትአደጋ የሚያስከትል እናአፋጣኝ የጽኑ ህክምና (ICU/Emergency care) የሚያስፈልገው ሁኔታነው!
አፋጣኝ የህክምና እርዳታ የሚሹ አስቸኳይ ምልክቶች (Red Flag Symptoms):
- ደረትላይ የሚሰማ ከፍተኛ ህመም ወይም መወጠር
- ከፍተኛየትንፋሽ እጥረት
- የሰውነትመስነፍ ፣ የፊት መጣመም ወይም የንግግር መደናቀፍ (የስትሮክ/Stroke ምልክቶች)
- ከፍተኛጭንቅላት ህመም ከማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ጋር
- የዓይንእይታ በድንገት መታወክ ወይም ማጣት
5. የደም ግፊት የሚያስከትላቸው ከባድ የጤና ጉዳቶች (Complications)
ክትትል እና ህክምና ካልተደረገ የደም ግፊት በሚከተሉት የሰውነት ክፍሎች ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል፡
- በልብላይ (Cardiovascular System):
- የልብ ድካም (Heart Attack): የልብ ደምቧንቧዎች በመጥበባቸው የሚከሰት።
- የልብ ስራ ማቆም (Heart Failure): ልብ ደምለመግፋት ከመጠን በላይበመጨነቁ ምክንያት የሚፈጠር።
- በአንጎልላይ (Cerebrovascular System):
- ስትሮክ (Stroke):በአንጎል ውስጥ የደምቧንቧ በመዘጋቱ ወይምበመፍንዳቱ የሚከሰት የሽባነትአደጋ።
- በኩላሊትላይ (Renal System):
- የኩላሊትደም ቧንቧዎችን በመጉዳትለዘላቂ የኩላሊት ድካም (Chronic Kidney Disease) መዳረግ።
- በዓይንላይ (Ocular System):
- የዓይንደም ቧንቧዎችን በመጉዳትለእይታ ማጣት (Retinopathy) ማጋለጥ።
መልእክት (Take-Home Message):
የደም ግፊት ምልክት እስኪያሳይ አይጠብቁ! ግፊትዎን ዘወትር ይለኩ፣ የህክምና ባለሙያ መመሪያዎችን ይከተሉ፣ እንዲሁም ድንገተኛ ምልክቶች ሲታዩ ሳይዘገዩ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ህይወትዎን ይታደጉ።
(ማስታወሻ፡ይህ መረጃ ለትምህርታዊ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዓላማ ብቻ የተዘጋጀ ነው።)
Eshetayehu Worku
Emergency and Critical Care Nurse Specialist (MSc), Wecare Health Consultant




