የመገጣጠሚያ እብጠት (Ganglion Cyst) ምንድነው?

Ganglion Cyst (ጋንግሊዮን ሲስት) አብዛኛውን ጊዜ በመገጣጠሚያዎች ወይም በጅማቶች አቅራቢያ የሚወጣ በፈሳሽ የተሞላ ምንም ጉዳት የሌለው እብጠት ነው። ብዙ ጊዜ በእጅ ላይ የሚታይ ሲሆን፣ መጠኑም እንደ ጊዜው እና ምክንያት ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል። በመገጣጠሚያ ወይም በጅማት ሽፋን ላይ በፈሳሽ የተሞላ እብጠት ሲሆን ይህ ዕብጠት ጥቅጥቅ ካሉ ተያያዥ ቲሹዎች፤ ከጅማት ሽፋኖች፣ ከራሳቸው ከጅማቶች፣ እንዲሁም ከመገጣጠሚያ ሽፋኖች፣ መነሻቸውን አድርገው ይከሰታሉ ተብሎ ይታሰባል።
ይህ እብጠት እነማን ላይ ሊከሰት ይችላል?
Ganglion cysts በጣም ከተለመዱ የእጅ ላይ ቲሹ ዕጢዎች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀስ ሲሆን ይህ ዕብጠት በሁሉም ዕድሜዎች ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በዋነኝነት ግን እድሜያቸው ከ 20-40 ዓመት የሆኑት 70% ያህል ተጋላጭ መሆናቸውን አንዲሁም በጾታዊ ክፍፍል ሲታይ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ይበልጥኑ ተጋላጭ መሆናችውን ጥናቶች ያመለክታሉ።
ይህ ችግር እድሜያቸው ከ 10 አመት በታች የሆኑ ህፃናት ላይ በብዛት ላይስተዋል ይችላል።
የመገጣጠሚያ እብጠት (Ganglion Cyst) በብዛት የት ይከሰታል?
ይህ ዕብጠት ብዙውን ጊዜ በእጃችን አንጓ መገጣጠሚያ ጀርባኛው ክፍል ላይ የሚከሰት ሲሆን አንዳንዴም በእጃችን አንጓ መዳፍ ላይም ሊታዩ ይችላሉ።
በእጃችን የጀርባ አንጓ ዕብጠቱን በደንብ ለማስተዋል, የእጃችን አንጓን ወደ ፊት በማጠፍ በይበልጥ በደንብ ለማየት ይረዳል።
ይህ እብጠት በተለምዶ የእጅ መገጣጠሚያ ላይ ይስተዋል እንጂ ባልተለመደ መልኩ የታችኛው የጣቶቻችን ክፍል ላይ ፤የጣቶቻችን ጫፍ ላይ ፤ጉልበት እና ቁርጭምጭሚት አካባቢ እንዲሁም የታችኛው የእግራችን አናት ላይ ሊታዩ ይችላሉ።
Ganglion Cyst መንስኤው ምንድነው?
መንስኤው ብዙውን ጊዜ ባይታውቅም በተደረጉ ጥናቶች መሰረት መገጣጥሚያ ላይ በሚፈጠር ተደጋጋሚ ጫና ፈሳሽ አመንጭ ሕዋሳት (Mucin Cells) ምርታችውን አንዲጭምር በማድረግ ፈሳሽ ወደ ውጭኝው የሽፋን ክፍል በመሄድ አንዲከማች ሆኖ ለስላሳ፣ ክብ፣ የሚንቀሳቀስ እብጠት ሆኖ በመገጣጠሚያ (በተለይ የእጅ የጀርባ አንጓ) ይቀመጣል።
አጋላጭ ሁኔታዎች
- በእጅ አንጓ ወይም በጣት መገጣጠሚያ ላይ ጉዳት ሲያጋጥም
- በጅማቶች ወይም በመገጣጠሚያዎች ላይ ብግነት መኖር
- የእጅ አንጓዎችን እና ጣቶችን የሚጠቀሙ ተደጋጋሚ እንቅስቃሴዎች ማረግ
- ሥር የሰደደ በሽታ ፣ ለምሳሌ ቁርጥማት
Ganglion Cyst ለመሆኑ ምልክቶቹ ምንድናችው?
ዋና ዋና ምልክቶች፦
ቅርጽ፦ ክብ ወይም ሞላላ የሆነ እብጠት። ለመዳሰስ በምንሞክርበት ወቅት ጠንካራ፣ ለስላሳ፣ ክብ፣ የሆነ እብጠት በመገጣጠሚያ (በተለይ የእጅ አንጓ) ልናስተውል እንችላለን።
ህመም፦ ብዙውን ጊዜ የህመም ስሜት ባይኖረውም አልፎ አልፎ፣ እብጠቱ የነርቭ መጨናን ካመጣ ህመምን ከማስከተል ባሻገር እዛ አካባቢ ሲነኩ ስሜት ከማጣት sensory loss እስከ ጣቶችን ማንቀሳቀስ አለመቻል፣ የመደንዘዝ ወይም የጡንቻ መድከም ስሜት ሊፈጥር ይችላል።
መጠን ፦ የእብጠቱም መጠን በጊዜ ሂደት መለዋወጥ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ መቻን እና የመሳሰሉት በዋነኝነት ከምልክቶቹ ውስጥ ይካተታሉ።
Ganglion Cyst ህክምናው ምንድነው?
1) Conservative Management
ከእብጠቱ በቀር ምንም አይነት የህመም ምልክት ማይታይ ከሆነ ምንም አይነት ህክምና ሳያስፈልገው በራሱ የመጥፋት እድሉ 58% ሲሆን እስከ አንድ አመት ጊዜም ሊወስድ ይችላል። ህመሙ ከባድ ከሆነ እንደ አይቦፕሮፊን አይነት የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ሊወሰድ ይችላል።
2) Temporarily Brace (የመገጥጠሚያ ድጋፍ)
እብጠቱ ያለበት ቦታ ላይ የሚደረግ የመገጥጠሚያ ድጋፍ (Temporarily Brace) ለረጅም ጊዜ ይህንን መጠቀም የጡንችዎች መቀጭጭ የመገጠጥሚያ በቋሚነት አለመንቀሳቀስ ሊያስከትል ስለሚችል ብዙ ጊዜ አይመከርም
3) Ganglion Cyst Aspiration (የእብጠቱን ፈሳሽ ቀድቶ ማውጥት)
እብጠቱ ላይ ያለውን ፈሳሽ ቀድቶ ማውጥት (Ganglion Cyst Aspiration) ሌላው አማራጭ ሲሆን ከዚህ ህክምና በሑላ በእንድ አመት ውስጥ ተመልሶ የመምጥት እድሉ ከፍተኛ ነው
4) Ganglion cyst Excision (በቀዶ ጥገና እብጥቱን ቆርጥ ማውጥት)
በቀዶ ጥገና እብጥቱን ቆርጥ ማውጥት (Ganglion cyst Excision) ይህ የመጨረሽው እማራጭ ሲሆን ሙሉ ተቆርጥ መውጥቱን እርግጥኝ መሆን ይኖርብናል። ይህም ተመልሶ የመምጣት እድልን እንዲቀንስ ይረዳል።




