በምጥ ጊዜ ስለሚሰጥ ህመም ማስታገሻ ምን ያህል ያውቃሉ?
የ epidural የህመም ማስታገሻ የማደንዘዣ አይነት ሲሆን ከእንብርት እስከ የላይኛው እግር ክፍል የመደንዘዝ ስሜት በመፍጠር የሚሰራ የማደንዘዣ አይነት ነው። በምጥ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ንቁ ሆነሽ እንድታምጪ እና በምጥ ወቅት የሚሰማ ወደታች መግፋት እንዲሰማሽ ያስችላል፤ይህም በሁለተኛ የምጥ ክፍል ላይ የግፊት ስሜት መኖሩን በመረዳት ለማማጥ ያስችልሻል።
- የepidural ማደንዘዣ በምጥ የመጀመርያው ክፍል የሚሰጥ ሲሆን ከተሰጠ በ15 ደቂቃ ውስጥ ይሰራል።ማደንዘዣ ከተሰጠ በሁዋላ የእግር መደንዘዝ ሊኖር ይችላል፡በተጭማሪም ለጽንሱ እና ለእናቲቱ ጤንነት ሲባል ቀጣይነት ያለው ክትትል ይደረጋል።
የepidural ማደንዘዣ ለማን አይሰጥም?
- የደም መርጋት ላለባት
- ለመውለድ የተቃረበቅች
- የደም ግፊት የቀነሰ ከሆነ
- በሰውነት ውስጥ ኢንፌክሽን ካለ
- አንዳድ የነርቭ ችግሮች ካሉ ለምሳሌ spinal aneurysm
- አንዳንድ የልብ ህመሞች ካሉ
የepidural ጥቅሞች
- በአብዛኛው ውጤታማ ነው
- ከepidural በሁዋላ አልጋ ላይ ሆነሽ መንቀሳቀስ ትችያለሽ
- የመግፋት ስሜት ሲመጣ መግፋት ትችያለስ
- ረዝም የምጥ ሰአት ከሆነ በመሀል እረፍት እንድታረጊ እና እንድትተኚ ይረዳሻል
የepidural የጎንዮሽ ጉዳቶች
- የደም ግፊት መቀነስ
- የወገብ ህመም-የተውጉበት ቦታ ለተወሰኑ ቀናት ህመም ሊኖረዉ ይችላል።
- የራስ ምታት
- ማቅለሽለሽ
- የሰውነት ማሳከክ
- እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት
- ኢንፌክሽን
- የምጥ ሰአት መርዘም




