የመራቢያ አካላት የፈንገስ ኢንፌክሽን

Bethel Dereje
Jul 8, 2025
undefined

አንዲት ሴት በህይወቷ ቢያንስ አንድ ግዜ የመራቢያ አካላት የፈንገስ ኢንፌክሽን ሊገጥማት ይችላል። 90 ከመቶ የሚሆነው ኢንፌክሽን ካንዲዳ አልቢካንስ(Candida albicans) በሚባለው የፈንገስ ዝርያ ምክንያት ይከሰታል። ይህ የፈንገስ ዓይነት በሰውነታችን ውስጥ በጥገኝነት የሚኖር ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙ ሲዳከም ኢንፌክሽን ሊያመጣ ይችላል።

 

ምክንያቶቹ

አጠቃላይ የሆኑ የሰውነት ህመሞች -  የስኳር ህመም፡ ኤች አይ ቪ ፡ ከመጠን በላይ ውፍረት

እርገዝና ፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች(ኢስትሮጅን ያላቸው)

መድሃኒቶች(antibiotics, steroids)

ለረዥም ጊዜ የቆየ ህመም(chronic disease)

 

ምልክቶቹ

ማሳከክ

ማቃጠል ወይም መላጥ

አይብ የሚመስል ወፍራም ፈሳሽ(ሽታ ሊኖረው ይችላል)

የሽንት ማቃጠል

በግነኙነት ሰዓት ህመም።

 

ምርመራው

የማህጸን ፈሳሹ ተወስዶ ፈንገሱ መኖሩን ማረጋገጥ

 

ሕክምናው

  1. መንስኤዎቹን መቆጣጠር። ለምሳሌ የስኳር ህመም ካለባቸው የስኳሩን ቁጥጥር ማስተካከል፣ ከመጠን በላይ ውፍረት ካላቸው የሰውነት ክብደታቸውን ማስተካከል፣ የሚወስዱት መድሃኒት መቆም የሚችል ከሆነ ማቆም። አንዳንድ ሰዎች ሳይታዘዝላቸው የሚወስዱትን ይጨምራል።
  2. መድሃኒቶች፤ የሚቀባ፣ በማህጸን የሚገባ፣ የሚዋጥ ወይንም የተቀመመ መታጠቢያ ሊሆን ይችላል።

 

እንዴት እንከላከለው? 

የታወቀ የቆየ ህመም ካለ መጀመሪያ እሱን መቆጣጠር (ስኳር፡ኤች አይ ቪ)

በግድ የለሽነት የሚወሰዱ መድሃኒቶችን ማቆም

የሚወስዱትነ የወሊድ መከላከያ ዘዴ መቀየር

የሚጠቀሙትን የውስጥ ሱሪ ቢቻል ከኮተን የተሰሩ ቢሆኑ

ንፅህናን ለመጠበቅ ውሃ ብቻ መጠቀም

ሱሪ የሚያዘወትሩ ከሆነ ቀሚስ መልበስ በጭን መሃል የሚፈጠረውን ሙቀት ለመቀነስ ይረዳል።

Comments (1)

Muna Yitaktu
Jul 9, 2025

Thank you Dr. This is very informative.