ፖኦሊ ሲስቲክ ኦቫርያን ሲንድረም እና መካንነት
(Polycystic ovarian syndrome and infertility)
በመውለድ እድሜ ላይ ያሉ ሴቶችን የሚከስት የተለመደ የሆርሞን በሽታ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በጉርምስና የእድሜ ክልል ወቅት ነው፤ነገር ግን ምልክቶቹ በጊዜ ሂደት ሊለዋወጡ ይችላሉ።
PCOS የሆርሞን መዛባት፣ መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ፣ ከመጠን በላይ የሆነ androgen መጠን እና በእንቁልጢ ውስጥ ዉሃ የቋጠሩ እባጮች (cysts) ሊያስከትል ይችላል። መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ፣ አብዛኛውን ጊዜ የእንቁላል መመረት ባለመኖሩ እርጉዝ መፈጠር እድል ይቀንሳል። PCOS የመሃንነት ዋነኛ መንስኤ ነው።
PCOS ሙሉ ለሙሉ ሊያድን የሚችል መድሃኒት የሌለው ሥር የሰደደ በሽታ ነው እናም ሊታከም አይችልም። ነገር ግን፣ አንዳንድ ምልክቶች በአኗኗር ዘይቤ ለውጥ፣ በመድሃኒት እና በመሃንነት ህክምናዎች ሊሻሻሉ ይችላሉ።
ከ6-13% የሚሆኑ በመውለድ እድሜ ላይ ያሉ ሴቶችን ላይ ተጽእኖ ያሳድራል, እና እስከ 70% ከሚሆኑት ይህ ህመም ያለባቸዉ ሴቶች ይህ ህመም እንዳለባቸው አያቁም።
የ PCOS ህይወታዊ እና ስነ ልቦናዊ ተፅእኖዎች፣ በተለይም ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ የሰውነት ገጽታ እና መሃንነት ጋር የተያያዙ፣ የአእምሮ ጤና ተግዳሮቶችን እና ማህበራዊ መገለልን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ምልክቶች
የ polycystic ovary syndrome ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው ሊለያዩ ይችላሉ። ምልክቶቹ በጊዜ ሂደት ሊለወጡ ይችላሉ እና ብዙ ጊዜ ያለ ግልጽ መነሻ ምክንያት ይከሰታሉ።
- ከፍተኛ ህመም ያለው፣ የተዛባ የወር አበባ ኡደት
- መሃንነት
- ብጉር ወይም ቅባት ያለው ቆዳ
- በፊት ወይም በሰውነት ላይ ከመጠን በላይ ፀጉር
- የወንድ-ላይ የሚከሰት አይነት ራሰ በራነት ወይም የፀጉር መሳሳት
- ክብደት መጨመር, በተለይም በሆድ አካባቢ
ፒሲኦኤስ ያለባቸው ሰዎች የሚከተሉትን የጤና እክሎች የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
- የስኳር በሽታ
- የደም ግፊት (ከፍተኛ የደም ግፊት)
- ከፍተኛ ኮሌስትሮል
- የልብ ሕመም
- endometrial ካንሰር (የማህፀን ውስጠኛው ሽፋን ካንሰር)
ፒሲኦኤስ ጭንቀትን፣ ድብርት እና አሉታዊ የሰውነት ገጽታን ሊያስከትል ይችላል። አንዳንድ ምልክቶች እንደ መካንነት፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ያልተፈለገ የፀጉር እድገት ወደ ማህበራዊ መገለል ሊመሩ ይችላሉ። ይህ እንደ ቤተሰብ፣ ግንኙነት፣ ስራ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የመሳሰሉ ሌሎች የህይወት ዘርፎችን ሊነካ ይችላል።
ህክምናው
ለ PCOS ምንም መድሃኒት የለም፤ነገር ግን ህክምናዎች ሊያሻሽሉ ይችላሉ።
የወር አበባቸው ያልተስተካከለ፣ ለማርገዝ የተቸገሩ ወይም ከመጠን በላይ የሆነ ብጉር እና የፀጉር እድገት ያለባቸው ሰዎች የጤና ባለሙያን ማነጋገር አለባቸው።
አንዳንድ የ PCOS ምልክቶች በአኗኗር ለውጦች ሊቀነሱ ይችላሉ። ጤናማ አመጋገብ መመገብ እና በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ እና ለአይነት 2 የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ያስችላል።
የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች (የወሊድ መከላከያ ክኒን) የወር አበባ ዑደትን ለመቆጣጠር እና ምልክቶችን ለመቀነስ ይረዳሉ።ሌሎች መድሃኒቶች በ PCOS ምክንያት የሚመጡትን ብጉር ወይም ያልተፈለገ የፀጉር እድገትን ይቀንሳሉ።
በፒሲኦኤስ ምክንያት ለመካንነት የሚሰጡ ሕክምናዎች የአኗኗር ለውጦችን፣ መድኃኒቶችን ወይም የቀዶ ጥገናን መደበኛ እንቁላል መለቀቅን ለማነቃቃት ይረዳሉ። In-vitro fertilization (IVF) ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።




