የወር አበባ ህመም መቆጣጠር  - ከወር አበባ ሕመም ለመገላገል የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች

Melat Geatchew
Mar 12, 2026
undefined

የወር አበባ ህመም መቆጣጠር  - ከወር አበባ ሕመም ለመገላገል የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች

የምግብ ፍላጎት መጨመር፣ የእንቅልፍ ማጣት ወይም መዛባት፣ የሆድ መነፋት፣ የስሜት ለውጦች (ብዙውን ጊዜ ብስጭት)፣ ድካም፣ የጡት መጠንከርና መጠን መጨመር ከሚስተዋሉ የወር አበባ ምልክቶች ጥቂቶቹ ናቸው።  በወር አበባ ወቅት የወር አበባ ቁርጠት ከስምንት ሴቶች መካከል አንዷን ያጋጥማታል። ቁርጠት ከሚያጋጥማቸው ሴቶች መካከል አንዷ ከሆንሽ፤ የወር አበባ የምታይባቸው ቀናቶች ምናልባት ላንቺ የወሩ ከባድ ቀኖች ሊሆኑብሽ ይችላሉ። የወር አበባ ህመም በማንኛዋም ሴት ላይ ሊከሰት የሚችል ነገር ግን ቸል መባል የሌለበት ነገር ነው። በቤት ውስጥ ያሉ ቀላል መፍትሔዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። 

 የወር አበባ ቁርጠት እንዲከሰት የሚያደርገው ምንድን ነው?

በወር አበባ ጊዜ ቁርጠት የሚከሰተው ለምን እንደሆነ ለመረዳት ወደ ኋላ በመመለስ በመጀመሪያ የወር አበባ ለምን እንደምናይ ማጤን ጠቃሚ ነው። 

አንዲት ሴት ለአቅመ ሄዋን ከደረሰች ጀምሮ የመራቢያ አካላት ማለትም እንቁልጢ እና የማህጸን ግድግዳ ለ እርግዝና ይዘጋጃል ፣ ይህም የሚሆነው ፕሮጀስትሮን በሚባለው ሆርሞን አማካኝነት ነው ፣ የዚህ ሆርሞን መጠን መጨመር ለ እርግዝና የተመረጠውን መልካሙን  ማዳበር እና የማህጸን ግድግዳ ጽንሱን ለማሳደግ እንዲረዳው ያጎለብተዋል ፣ በትናንሽ ድም ስሮችም እንዲገነባ ያደርገዋል ነገር ግን በወሩ ወይንም ለቀናት የወንድ የዘር ፍሬ ሲጠብቅ የነበር የዳበረ እንቁላል ምንም አይነት የዘር ፊረ ካላገኘ እና ጽንስ ካልተፈጠረ የዳበረው እንቁላል እና የማህጸን ግድግዳ ፕሮስታግላንዲን የተባለው ሆርሞን ስለሚቀንስ በተፈጠሮ እንዲወገድ እና የወር አበባ እንዲፈጠር ያደርጋል።

ይህ የተለመደ የመራባት ዑደት የሴቷ አካል በየወሩ ለእርግዝና ዝግጁ ይሆናል። ምናልባት በዚህ የመራባት ሂደት ውስጥ በጣም የታወቀው የወር አበባ ነው። (አንዳንድ ጊዜ ፔሬድ ተብሎም ይጠራል)።  ይህም ማህፀን ግድግዳውን ሲያሶግድ ወይም ሲፈርስ የሚፈጠር ነው። የዚህ ሂደት ዓላማው ማህፀን የዳበረ እንቁላል ለመቀበል እና ለመመገብ እንዲዘጋጅ መርዳት ነው።  ከማህፀን ውስጥ ደምና ሕብረ ሕዋስ (ቲሹ) በፈሳሽ መልክ ይወጣሉ ወይም ይወገዳል።  ይሁን እንጂ የወር አበባሽ ቀለል ያለ ከሆነ ከቀላል መረበሽ እስከ ከባድ ሕመም (ቁርጠትን ጨምሮ) ምልክቶች ጋር ፔሬድ ሊመጣ ይችላል። 

 

በማህፀን ውስጥ የሚገኙት ጡንቻዎችና የደም ሥሮች የማህፀን ግድግዳን ለማፍረስ ሲሉ ይኮማተራሉ ወይም ይጨማደዳሉ። የእነዚህ መኮማተር በታችኛው የሆድ ክፍል እና በጀርባ ላይ ቁርጠትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።  እነዚህ የማህጸን መኮማተሮች ፕሮስታግላንዲን በተሰኘው ሆርሞን አማካኝነት ይከሰታሉ። ይህም ከወር አበባ መምጣት እና በወር አበባ ወቅት ለሚኖሩ አለመመቸቶች እና ህመሞች ምክኛት ሊሆን ይችላል። የወር አበባ ቁርጠት ለተለያዩ ሴቶች የተለያየ ስሜት ሊፈጥር ይችላል። አንዳንዶቹ መጠነኛ ምቾት ማጣት ብቻ ያላቸው ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ የዕለት ተዕለት ሥራዎችን አስቸጋሪ የሚያደርግባቸው ከባድ ሕመም ያጋጥማቸዋል። ከሦስት እስከ ሰባት ቀናት የሚቆየው የወር አበባሽ ካለፈ በኋላ፤ የማህፀን ግድግዳ እንደገና  ለሚቀጥለው ሳይክል ማደግ ይጀምራል በተጨማሪም ይወፍራል። ከጊዜ በኋላም ኦቪውሌሽን ይከሰታል። 

ከኦቪውሌሽን በኋላ ወደ ጽንስ የተቀየረ እንቁላል ከሌለ፤ የወር አበባ ዑደትን እንደገና ለመጀመር ጊዜው አሁን መሆኑን ለሰውነትሽ ምልክት ይሰጣል። እናም የወር አበባ ዑደቱ ይቀጥላል። 

 በቤት ውስጥ የወር አበባ ቁርጠትን በፍጥነት እንዴት ማስታገስ ይቻላል

 

በወር አበባ ጊዜ ከሚከሰት ቁርጠት እፎይታ ለማግኘት የሚረዱ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው:-

1️⃣ ሙቅ ነገር መያዝ

ሙቀት ለቁርጠት አስተዋጽኦ የሚያደርጉትን ጡንቻዎች ዘና ለማድረግ ይረዳል፤ ስለዚህ በሆድዎ ወይም በጀርባዎ ላይ ሙቀትን ማድረጉ ህመምዎን ለማስታገስ ይረዳል። ለብ ያለ ውሀ በውሀ ኮዳ ወይም ተመሳሳይ እቃዎች የታችኛው የሆድ ክፍል ላይ በመያዝ የጡንቻ መኮማተርን መቀነስ ይቻላል ። ማሞቂያ ፓድን (Heating Pads) መጠቀም ወይም በሞቀ ውሃ ገላ መታጠብ ወይም መንከር የወር አበባ ህመምን ለማስታገስ ጥሩ መንገዶች ናቸው። 

2️⃣ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ይውሰዱ

የወር አበባ ቁርጠት የሚያሠቃይ ስለሆነ፣ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች የመፍትሄዎች አካል መሆናቸው ግልጽ ነው። ለወር አበባ ህመም፣ NSAIDs (ስቴሮይድ ያልሆኑ ፀረ-ኢንፍላማቶሪ መድኃኒቶች) ፕሮስጋንዲንን ስለሚቀንሱ በተሻለ ሁኔታ ሊሠሩ ይችላሉ። ፕሮስታግላንዲን:- የወር አበብ ቁርጠትን የሚያስከትለው የጡንቻዎች መኮማተር የሚያነሳሳ ሆርሞን ነው። 

ኢቡፕሮፌን (አድቪል)እና ናፕሮክሲን (Ibuprofen (Advil) and naproxen (Aleve)) የ NSAIDs መድሃኒት ምሳሌዎች ናቸው። በመመሪያው መሰረት እያንዳንዱን መድሃኒቶች መውሰድዎን ያረጋግጡ። 

በተጨማሪም፤ አሲታሚኖፊን (ታይሊኖል) (Acetaminophen (Tylenol)) የወር አበባ ህመምን ለማስታገስ ይረዳል፤ ነገር ግን ለከባድ የወር አበባ ቁርጠት አስተዋጽኦ የሚያደርገውን ኢንፍላሜሽን እንዳይኖር አይከላከልም። 

 

3️⃣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

ህመም ሲሰማዎ ዘና ማለት እና ትንሽ እረፍት ማድረግ የተሻለ እንደሆነ ይሰማዎት ይሆናል። ነገር ግን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተፈጥሯዊ የህመም ማስታገሻ ነው። 

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ኢንዶርፊን (endorphins) እንዲለቀቅ ያበረታታል፤ እነዚህም በሰውነት የሚመረቱ ኬሚካሎች ሲሆኑ የህመም ስሜትን የሚገድቡ ናቸው። 

በተጨማሪም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጭንቀትን ለመቀነስ ጥሩ መንገድ ነው። ይህም በሚሰማዎት የህመም ስሜት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። 

 

4️⃣ ጭንቀትን ለመቀነስ እርምጃዎችን ይውሰዱ

ጭንቀት በብዙ መንገዶች በሰውነትዎ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፤ ይህም የህመም መዳረሻ ገደብ ዝቅ ማድረግን ይጨምራል። 

ጭንቀትን ወይም ውጥረትን ለመቀነስ ከስራው ይልቅ ማውራቱ ቀላል ነው፤ ነገር ግን ይህን ለማድረግ እርምጃዎችን መውሰድ ከወር አበባ ቁርጠት እፎይታ ለማግኘት ይረዳዎታል። በቂ የሆነ እፍረት እና እንቅልፍ ሰውነትን ህመምና ድካምን እንዲቋቋም ይረዳዋል

ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተጨማሪ ጭንቀትን ለመቀነስ የሚረዱ በርካታ መንገዶች ከዚህ በታች ቀርበዋል:-

🔸ዮጋ (Yoga)

🔸ጥልቅ የአተነፋፈስ ልምምድ (Deep Breathing Exercise)

🔸ጥሞና (Meditation)

🔸ዎክ ማድረግ (ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ )

 

5️⃣አመጋገብን ማስተካከል 

ውኃ በበቂ ሁኔታ መጠጣት፦ በቂ ውኃ መጠጣት በሰውነት ውስጥ ፈሳሽ እንዳይጠራቀምና የሆድ መንፋትን ለመቀነስ ይረዳል።

የአመጋገብ ለውጥ፦ ጨዋማ፣ ስብ፣ ካፌይን እና ጣፋጭ ምግቦችን መቀነስ፤ ይልቁንም አትክልትና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር።

 

በአይረን እና ማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦች ሰውነትን በወር አበባ ወቅት ያግዛሉ ። አንዳንድ ቫይታሚኖች እና ማዕድናት ቁርጠትን ለመቀነስ ስለሚረዱ ጤናማ አመጋገብን መመገብ የወር አበባ ህመምን ለማስታገስ ሌላኛው መንገድ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቲያሚን ተብሎ የሚጠራው ቫይታሚን ቢ-1 እና ማግኒዚየም የወር አበባ ቁርጠትን ለመቀነስ ይረዳሉ። 

እነዚህን ሁለት ቫይታሚኖችና ማዕድናት አብዛኛውን ጊዜ አዋቂዎች በጤናማ አመጋገብ አማካኝነት በብዛት ያገኟቸዋል። 

 

በቫይታሚን ቢ-1 እና ማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-

🔹ለውዝ 

🔹ያልተፈተገ ስንዴ

🔹ባቄላ፣ ምስር እና ሽንብራ

🔹ስፒናች (Spinach)

🔹የአበባ ጎመን

🔹ቆስጣ

🔹አቮካዶ እና 

🔹ብርቱካን ናቸው። 

የወር አበባ ቁርጠት ከባድ በሚሆንበት ጊዜ ምን ማድረግ አለብዎት

ከላይ የተጠቀሱት የወር አበባ ቁርጠትን ለማስታገስ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች ቢሆኑም ለሁሉም ሴቶች በተለይ ደግሞ ከባድ ቁርጠት ላላቸው ሴቶች ላይጠቅሙ ይችላሉ። 

በወር አበባዎ ወቅት ከባድ ህመም ካለባችሁ ከማህጸን እና ጽንስ  ሐኪ ጋር መነጋገር አስፈላጊ ነው። ሐኪምዎ ስለ ምልክቶችዎ እና ዑደትዎ ይጠይቁዎታል። ህመምዎን ለማስታገስ የሚረዱ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦችን፤ እንዲሁም የዳሌ ምርመራ ማድረግ እና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መድሃኒቶችን ሊያዝልዎ ይችላል። 

ለምሳሌ ያህል፣ አንዳንድ ጊዜ የወር አበባ ቁርጠትን እና ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ሕመምን ለማከም የሆርሞን መቆጣጠሪያ መድኃኒቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ። 

በተጨማሪም፤ በአንዳንድ ሁኔታዎች ከባድ የወር አበባ ህመም ከባድ የሆነ የጤና ችግር እንዳለ ምልክት ሊሆን ይችላል። 

የወር አበባ ህመም በዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ላይ ሊያስከትል ከሚችለው ጉልህ ተጽዕኖ ባሻገር፤ ቁርጠቱ በራሱ በአብዛኛው የህክምና ጉዳይ አይደሉም። ይሁን እንጂ ከባድ የወር አበባ ቁርጠት አንዳንድ ጊዜ ይበልጥ ከባድ በሆነ የማሕፀን ችግር ምክንያት ሊከሰት ይችላል። 

 

በአንዳንድ ሁኔታዎች፤ ከባድ የወር አበባ ቁርጠት የሚከተሉት ችግሮች ምልክት ሊሆን ይችላል:-

 

♦️ኢንዶሜትርዮሲስ (Endometriosis) – የማህፀን ሕብረ ሕዋስ በማህፀን ቱቦ፣ በማህፀን ወይም በዳሌ ግድግዳ ላይ ሲተከል ወይም ሲጣበቅ። 

♦️የማህፀን ፋይብሮይድስ (Uterine Fibroids) – ህመም ሊያስከትሉ የሚችሉ ካንሰር ያልሆኑ የማህፀን እድገት ነው። 

♦️አዴኖሚዮሲስ (Adenomyosis) – የማህፀን ሕብረ ሕዋስ ወደ ማህፀን ጡንቻ ግድግዳነት ሲያድግ የሚፈጠር ነው። 

♦️ፐልቪክ ኢንፍላማቶሪ በሽታ (Pelvic inflammatory disease) – የማህፀንዎ፣ የፋሎፒያን ቱቦ እና/ወይም የእንቅላል ከረጢት ኢንፌክሽን ነው። 

 

ከላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች ውስጥ ጥቂቶቹ የመራባት እድልን ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ በተጨማሪም የተሳካ እርግዝና የማግኘት እድሎች ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ።

Comments (0)