የኃይል መጠጦች ለጤና ደህንነታቸው የተጠበቀ ናቸው?
የኃይል ሰጪ መጠጦች በመጠኑ እና በአግባቡ ሲወሰዱ ለአብዛኞቹ ጤናማ ጎልማሶች ደህና ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ከመጠን በላይ መጠጣት ግን ለከፍተኛ የጤና ችግሮች ያጋልጣል።
የኃይል ሰጪ መጠጦችን (Energy drinks) ከመጠጣት መቆጠብ ያለባቸው እነማን ናቸው?
አብዛኛዎቹ አዋቂዎች የኃይል ሰጪ መጠጦችን በመጠኑ መውሰድ ቢችሉም፣ አንዳንድ ሰዎች ግን ከእነዚህ መጠጦች መቆጠብ አለባቸው። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
ህጻናት እና ታዳጊዎች
እርጉዝ የሆኑ ወይም የሚያጠቡ ሴቶች
ለካፌይን (caffeine) ስሜታዊነት ያላቸው ሰዎች
የጤና ችግር ያለባቸው ወይም ከኃይል ሰጪ መጠጦች (energy drinks) ግብዓቶች ጋር ሊጋጩ የሚችሉ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎች
የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች
የልብ ችግር ያለባቸው ሰዎች
ለጭንቀት እና ሱሰኛ የመሆን አደጋን ያስከትላል።
የጤና አደጋዎች
ከፍተኛ ካፌይን፦ የልብ ምትን ይጨምራል።
ብዙ ስኳር፦ የክብደት መጨመርን ያመጣል።
የእንቅልፍ ማጣት፦ እንቅልፍን ይረብሻል።
ቸል ሊባሉ የማይገቡ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች
የኃይል ሰጪ መጠጦችን (energy drinks) በቋሚነት የሚወስዱ ከሆነ፣ ከመጠን በላይ እየወሰዱ መሆኑን የሚያሳዩ እና ችላ ሊሏቸው የማይገቡ አንዳንድ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-ከመጠን በላይ የካፌይን መጠን መውሰድ።
የመተንፈስ ችግር
ግራ መጋባት
ቅዠት (እውነት ያልሆኑ ነገሮችን ማየት ወይም መስማት)
የሚጥል በሽታ
ከመጠን ያለፈ ጥማት ወይም ሽንት መሽናት
ፈጣን ወይም ያልተስተካከለ የልብ ምት
የጡንቻ መወጠር ወይም መንቀጥቀጥ
ተቅማጥን፣ ማቅለሽለሽን ወይም ማስታወክን ጨምሮ የምግብ መፈጨት ሥርዓት መረበሽ
ማዞር ወይም መረበሽ
በንቃት ሁኔታ ላይ የሚታዩ ለውጦች
የኃይል ሰጪ መጠጦች (Energy drinks) አማራጮች
ካፌይን መውሰድ እየፈለጉ ነገር ግን ከኃይል ሰጪ መጠጦች ሊመጡ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ማስወገድ ከፈለጉ፣ ይበልጥ ጤናማ የሆኑ አማራጮችን መምረጥ ይችላሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
ቡና
ሻይ
ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በፊት የሚወሰዱ ተጨማሪ ምግቦች (Pre-workout supplements)
የማይመከሩላቸው አካላት
ሕፃናት እና ታዳጊዎች
እርጉዝ እና አጥቢ እናቶች
የልብ ሕመም ያለባቸው ሰዎች




