የወር አበባ ከመጀመሪያው ጀምሮ አለማየት (primary amenorrhea)
የወር አበባ መቅረት( Amenorrhea ) ማለት ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ የወር አበባ ሳይታይ መቅረት ማለት ነው።
የወር አበባ ከመጀመሪያው ጀምሮ አለማየት (Primary Amenorrhea) ማለት ፦ አንዲት ሴት ልጅ ዕድሜዋ 15 ዓመት ደርሶ ምንም ዓይነት የወር አበባ ማየት ሳትችል ስትቀር፣ ወይም ጉርምስና( የአቅመ ሄዋን ) እንደ ጡት በማደግ ላይ ያሉ የመጀመሪያ ምልክቶች ከታዩ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የወር አበባ ማየት ሳትችል ስትቀር ማለት ነው ። ብዙውን ጊዜ በዘረመል ሁኔታዎች (አብሮ የተወለዱበት ሁኔታ) ወይም ከተወለዱ በኋላ የሚከሰቱ ሁኔታዎች (ከተወለዱ በኋላ የሚፈጠሩ ሁኔታዎች) ምክንያት የሚታይ የጤና ሁኔታ ነው ለዚህም የማህጸን ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር የህክምና ምርመራ እና ክትትል ያስፈልጋታል።
ለመጀመሪያው አይነት የወር አበባ መቅረት(primary amenorrhea)
መንስኤዎች እና መፍትሄዎች
መንስኤዎቹ - ለሁለት የማህፀን አወቃቀር ችግሮች (anatomical disorders) እና የሆርሞን መዛባት በማለት ይከፈላሉ።
ሀ- በተፈጥሮ የአወቃቀር ችግሮች ከሚጠቀሱት፦
- በሽል እድገት ጊዜ የሚከሰቱ ወደ ማህፀን ቱቦ ፣ዋናዉን የማህፀን ክፍል የማህፀን አፍ አና የላይኛዉን የከረቤዛ ክፍል (Mullerian defects) በተለያዩ ደረጃዎች ችግር ሲፈጠር ሲሆን በጣም ከፍተኛዉ ችግር ከላይ የተጠቀሱት ክፍሎች በአንዲት ሴት ላይ አለመኖር ይሆናል። በዚህም የተነሳ የወር አበባ ማየትም ሆነ ማርገዝ ላይ ችግር ይፈጥራል።
□ በሌላ በኩልም የቫጃይና ግድግዳ መሥራት (vaginal septum) የድንግልና መደፈን (imperforate hymen)ና የብልት የዉጨኛዉ ክፍል መጣበቅ (labial fusion) ለወርአበባ መቅረት መንሴዎች ሊሆኑ ይችላሉ። የተወሰኑት በህክምና ማስተካከል ይችላል።
ለ-ከሆርሞን መዛባት ከሚጠቀሱት ዉስጥ
1-የእንቁላል ማምረቻ አለማደግ ወይ መጎዳት (hypergonadotropic hypogonadism)
እነዚህም በዘረ መል ችግሮች (chromosomal abnormalities -gonadal dysgenesis) ወይም በኢንፌክሽን በጨረር ወይ ቀዶጥገና የማህፀን እንቁላል ማምረቻ ሲወጣ/ሲጎዳ የሚመጣ አይነት ሲሆን ምንም እንኳን ከእእምሮ ክፍል የሚመነጩት ሆርሞኖች ከፍ ቢሉም የእንቁላል ማምረች ለሆርሞኖቹ ትክክለኛ ግብረመልስ ስለማይሠጥ ችግሮች ይከሰታሉ።
2-ከአእምሮ ዉስጥ ለወር አበባ ኡደት የሚረዱ ሆርሞኖች አለመመረት (hypothalamic amenorrhea )
- የሆርሞን መዛባት በተለይ Follicular stimulation hormone -FSH ሙሉ ለሙሉ አለመመመረት (Kallmann syndrome) የወር አበባ ማስቀረትና በተለይ የማሽተት አለመቻልን አብሮ ያስከትላል።
- በተጨማሪም ይህን የአእምሮ ክፍል ከፍተኛ የስፖርት እንቅስቃሴ መስራት (excessive exercise)፣ከፍተኛ የአእምሮ ዉጥረት (stress) የወር አበባ ሊያስቀር ይችላል።
- በዚህም የእእምሮ ክፍል ዉስጥም የጨረር ጉዳት የካንሰር እጢ ሲከሰት ኢንፊክሽን ሲፈጥር የወር አበባን ሊያቆም ይችላል።
- በተጨማሪም የተለያዩ በሴቶች የመራቢያ አካላት ክፍሎች የሚፈጠሩ የሆርሞን መዛባቶች ለምሳሌም የታይሮይድ ሆርሞኖች መዛባት የፕሮላክቲን ሆርሞን መብዛት (hyperprolactinemia) የእንቁልጢ (የእንቁላል ማምረቻ) ሆርሞኖችን በተዛባ መጠን መለቀቅ (polycystic ovaries) ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ።
- ጉርምስና እና የአኗኗር ዘይቤ ምክንያቶች፡ ከፍተኛ መጠን ያለው የሰውነት ክብደት በፍጥነት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአትሌቲክስ ወይም የኤሮቢክስ እስፖርት ስልጠና ወይም ከባድ ጭንቀት።
የሚደረጉ ምርመራዎች
- የሕክምና ታሪክ እና አካላዊ፡ የእድገት ገበታዎችን፣ የጉርምስና ምልክቶችን እና የአኗኗር ዘይቤዎችን መፈተሽ።
- የላብራቶሪ ምርመራዎች፡ የእርግዝና ምርመራ፣ የሆርሞን መጠን (FSH፣ LH፣ Prolactin፣ እና TSH) እና የዘረ መል ምርመራ።
- የአልትራሳውንድ ምርመራ፡ የማሕፀንን፣ የማኅጸን ጫፍን እና እንቁላሎችን አወቃቀር ለመፈተሽ የሚደረግ ምርመራ።
ህክምና
የወር አበባ ከመጀመሪያው ጀምሮ አለማየት (primary amenorrhea) ሕክምና በጣም ግለዊ ፣ ከሰው ወደ ሰው የሚለያይ ነው ። ሙሉ በሙሉ በሕክምና ግምገማ ወቅት በተገኘው ዋና መንስኤ እና ምክንያት ላይ የተመሠረተ ነው። ይሄ ነው የሚባል የተለየ ወይም የሚሰጥ ህክምና ወይም ፈውስ የለውም።
ለምሳሌ ;- አካላዊ እገዳዎች ካሉ በቀዶ ጥገና በማረም፣ የሆርሞን መዛባት ካለ የሆርሞን ደረጃን ማመጣጠን ወይም የወር አበባን ለመቀስቀስ ጤናማ የሆኑ የአኗኗር ዘይቤዎችን ማስተካከል ነው።




