Learning materials for your health  Learn

ለብጉር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምንድናቸው?

  • September 22, 2021
  • የጤና እክሎች

ብጉር የቆዳ ቀዳዳዎች በሞቱ የቆዳ ሕዋሳት፣ በቅባት እና በባክቴሪያዎች ሲደፈኑ የሚፈጠር  የቆዳ ችግር ነው። 

ይህም 

  • ቆዳው እንዲቀላ፣ 

  • እንዲያብጥና 

  • እንዲቆጣ ያደርገዋል። 

በተገቢው ሁኔታ ያልታከመ ብጉር በቆዳ ላይ ጠባሳ በማምጣት የቆዳን ውበት ይቀንሳል፡፡ 

ለብጉር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

  • ዕድሜ፤ በተለይም በዓሥራዎቹ  የዕድሜ ክልል ውስጥ በጣም የተለመደ ነው፡፡

  • የሆርሞን ለውጦች፤ በጉርምስና  ወይም በእርግዝና ወቅት፤ 

  • በቤተሰብ ተመሳሳይ ታሪክ ካለ፤

  • የተወሰኑ መድኃኒቶች (Corticosteroids)

  • አመጋገብ፤ ከፍተኛ ቅባት ያላቸው ምግቦች ወይም ቸኮሌት አዘውትሮ መመገብ፤ ሆኖም ግን እስከአሁን ጠንካራ የሆነ ማስረጃ  አልተገኘም።

  • አንዳንድ ሕመሞች( Polycystic ovarian syndrome, Cushing syndrome)

  • ቅባት ወይም ቅባትነት የአላቸው ክሬሞች ወይም ኮስሞቲክሶች፡ ብጉር እንዲወጣ ሊያደርጉ ወይም ሊያባብሱት ይችላሉ፡፡

  • ውጥረት ወይም ጭንቀት፤  ቀደም ሲል የነበረን ብጉር የከፋ ሊያደርገው ይችላል።

ስለ ብጉር ምንነት እና ሕክምና ሙሉ መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

Share the post

scroll top